የከተሞች ጥግግት እና ስልጡ የመሬት አጠቃቀም፣

የከተሞች ጥግግት እና ስልጡ የመሬት አጠቃቀም፣
File Size:
6.09 MB
Date:
21 November 2019
Downloads:
307 x

 የየነገው ጊዜ የከተሞች ዘመን ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዚህ ዘመን አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጋ መቀበል እንዳለባት እሙን ነው፡፡ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽኑ እቅድ እና ሀገራዊው ራዕይ ላይ እንደተገለፀው ከተሞች የኢኮኖሚና ማህበራዊ የመዋቅር ሽግግር (structural transformation) ማዕከላትና የቀጣዩ የኢኮኖሚ ዘርፍ ምሰሶዎች እንደሚሆኑ ታምኖበታል፡፡  

የአንድ ሀገር ዕድገት በተለይም በዚህ በሉላዊነት ዘመን ከከተሞች ልማትና እድገት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ስለሆነ ከተሞች የእድገት ሞተሮች ናቸው ይባላል፡፡ ከዚህ እውነታ በመነሳትም ነው የከተማ ልማት ፖሊሲውም ሆነ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ከተሞች የገበያ፣ የኢንዱስትሪ፣ የመኖሪያና የአገልግሎት ማዕከላት ሆነው የከተሞችን ብቻ ሳይሆን የገጠሩንም ጨምሮ አጠቃላይ የሀገሪቱን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊና ፖለቲካዊ አጀንዳዎችን ለማሳካትና ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁልፍና ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የሚገልፁት፡፡ ምንም እንኳ ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘገምተኛ የከተሞች እድገት ላይ የቆየችና በአሁኑም ጊዜ በዝቅተኛ የከተማነት ደረጃ ላይ (20%) የምትገኝ ብትሆንም በቀጣይ 10 ዓመታት መካከለኛ ገቢ ላይ፣ በቀጣይም የበለፀገች ሀገር ለመገንባት ለምናደርገው ሁለገብ ሀገራዊ ጥረት ከተሞች የመሪነት ማዕከላዊ ሚና ይጫወታሉ፡፡ 

 
 
 
Powered by Phoca Download