የከተሞች የጎንዮሽ መስፋፋት፡ ምክንያቶች፣ ተጽዕኖዎች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች 

የከተሞች የጎንዮሽ መስፋፋት፡ ምክንያቶች፣ ተጽዕኖዎች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች 
File Size:
1.27 MB
Date:
21 November 2019
Downloads:
3009 x

ይህ “የከተማ ማስፋፊያ” ጥናት የፌደራል የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በጥልቀት እንዲጠኑ ከመረጣቸውና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ካከናወናቸው ሶስት ተያያዥ የከተማ ነክ ጥናቶች አንዱ ነው፡፡1 የጥናቱ አላማ ለጥናት በተመረጠው ርዕሰ-ጉዳይ ላይ አጠቃላይ የሁኔታዎች ዳሰሳ በማድረግ ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ ጉዳዮችን አንጥሮ ማውጣት ሲሆን፤ ይህም በአንድ በኩል በከተሞች አከባቢ ለሚከናወኑ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አካባቢያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ የመሬት ጥያቄዎችን ለማስተናገድ በከተማ አስተዳደሮች በኩል የሚደረጉትን ጥረቶች ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ፍትሃዊ እንዲሆኑ በማገዝ በሌላ በኩል ደግሞ ለዚህ ሲባል ከመሬት ይዞታቸው የሚነሱ አርሶ/አርብቶ አደሮች ከአጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴው ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ እንዳይሆኑ በማድረግ ከአጠቃላይ አገራዊ እድገትና የከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ በየከተሞቹ ለሚስተዋለው ከፍተኛ የመሬት ፍላጎት ተገቢውን ምላሽ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡ በመሆኑም ፈጣን ሁለንተናዊ እድገት በማስመዝገብ ላይ የሚገኙ ከተሞቻችን ቀልጣፋና ዘላቂ የሆነ የከተማ ቅርጽ (ሰስቴይኔብል አርባን ፎርም) እንዲኖራቸው ለማስቻል እንደሚረዳ ይታመናል፡፡  

በጥናቱ ስድስት ከተሞች በናሙናነት የተወሰዱ ሲሆን እነርሱም አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ደሴ-ኮምቦልቻ፣ መቀሌ፣ ሃዋሳ እና ጂማ ናቸው፡፡ እነዚህ ከተሞች የጥናቱን አላማ ለማሳካት በምክንያት የተመረጡ ሲሆኑ፤ ሁሉም ከተሞች በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን አገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር እንዲቻል በኢንዱስትሪ ልማት ማዕከልነት እንዲያገለግሉ በፌደራል መንግስቱ ተመርጠው ቅድመ ዝግጅትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተጀመረባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ከተሞች መጠነ-ሰፊ የማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴ የሚያስተናግዱ ሲሆን፤ የኢንዱስትሪ ልማቱን ተከትሎ በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ከፍተኛ እድገት እንደሚመጣ ይጠበቃል፡፡ በእነዚህ ከተሞች የሚጠበቀው ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የህዝብ ቁጠር እድገት የዚያኑ ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል የመሬት ፍላጎት እንደሚያስከትል እሙን ነው፡፡  

 
 
 
Powered by Phoca Download