የከተማ መልሶ ማልማት በኢትዮጵያ፡ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና የ ወደፊት አቅጣጫዎች

የከተማ መልሶ ማልማት በኢትዮጵያ፡ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና የ ወደፊት አቅጣጫዎች
File Size:
6.34 MB
Date:
21 November 2019
Downloads:
3200 x

ከተሞች ህይወት ያላቸው የሰው ልጆች መኖሪያ፣ መዝናኛና የሥራ ቦታ እንደ መሆናቸው መጠን ቅርፃቸውም ሆነ ውስጣዊ ይዞታቸው የቆረቆራቸውና የኖረባቸው ማህበረሰብ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ነፀብራቅ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተሞች ኡደታቸውን ጠብቀው ይወለዳሉ/ይቆረቆራሉ/፣ ያድጋሉ፣ ያረጃሉ፣ ይሞታሉ፣ በሥርዓት ከተመሩ ራሳቸውን ያድሳሉ አልያም ሞተው እስከ መጨረሻው ይጠፋሉ፡፡ የምዕራባውያን ከተሞች ያለፉበትን የዕድገት ፈለግ መሠረት አድርገው ሰፊ የምርምር ሥራ ያከናወኑ ፕሮፌሰር ሊዮን በርግ የተባሉ ምሁር ድምዳሜ ይህን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ እንደምሁሩ ግኝትና ድምዳሜ ከተሞች በሚከተሉት አራት የዕድገት ኡደቶች ውስጥ /Urbanization processes/ ያልፋሉ፡፡ 

የመጀመርያው ኡደት ከተሞቹ ከተቆረቆሩበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ የሚያልፉበትን ሂደት/urbanization process/ የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው የትራንስፖርት አገልግሎት መሻሻልን ተከትሎ የከተሞች ዕድገት ከመሃል ወደ ሳተላይት ከተሞች የሚያደርጉትን መስፋፋት /sub-urbanization/ ይመለከታል፡፡ ሦስተኛው ኡደት የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም አቅም ያላቸው ነዋሪዎች ወደ ከተማ ዳርቻ መሰደዳቸውን ተከትሎ የሚከሰተውን የዋናው ከተማ መውደቅ /dis-urbanization/ የሚመለከት ሲሆን የመሃል ከተማውን ውድቀት ለመታደግ ሲባል በሚወሰድ የከተማ ማደስ እርምጃ አማካይነት የሚፈጠረው የዋናው ከተማ ማንሰራራት /re-urbanization/ የመጨረሻው የከተሞች ዕድገት ኡደት ነው (በርግ፣ 1987)፡፡ 

 
 
 
Powered by Phoca Download