የሀገር ውስጥ የግል ባለሀብት በአምራች ኢንዱስትሪው ውስጥ የሞተርነት ሚናውን ከመጫዎት አኳያ ያሉት ተግዳሮቶች፣ ዕድሎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች

የሀገር ውስጥ የግል ባለሀብት በአምራች ኢንዱስትሪው ውስጥ የሞተርነት ሚናውን ከመጫዎት አኳያ ያሉት ተግዳሮቶች፣ ዕድሎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች
File Size:
3.07 MB
Author:
ዶ/ር አማረ ማተቡ | አቶ ካህሳይ ገረዚሄር | ዶ/ር ነፃነት ጆቴ | አቶ ደረጀ ራህመት | አቶ ዮናስ አብርሀ | አቶ ውባለም ስራው | አቶ አሸናፊ መሀሪ | አቶ አበበ ከበደ
Date:
10 October 2019
Downloads:
2661 x

አህፅሮተ-ማጠቃለያ (Executive Summary)

ሐምሌ 2009 ዓ.ም

መንግስት የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ጉልህ ሚና እንዲጫዎት የሚያስችሉ ሁኔታዎች አመቻችቷል፡፡ የተረጋጋ የማክሮ-ኢኮኖሚ ቀጣይነትን በማረጋገጥ ለልማታዊ የግል ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ተደርጓል፡፡ በተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተለይተው የተከለሉ የኢንዱስትሪ ዞኖችና ፓርኮች በማቋቋምና መሰረተ-ልማታቸው እንዲሟላ በማድረግ ለባለሀብቶች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን በአንደኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ውስጥ የተመዘገቡት ውጤቶች ቀደም ሲል ከነበረው የአምስት አመት የዕቅድ ዘመን አማካይ ጋር ሲነፃፀር የኢንዱስትሪው ዘርፍ እያደገ የመጣ ቢሆንም የአምራች ኢንዱስትሪው ከጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ግን ከ5% በታች መሆኑ ለዘርፉ ዕድገት ያለውን አስተዋፅኦ አነስተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

 
 
 
Powered by Phoca Download