ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2014
በኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት
- የተሽከርካሪዎች ጥገና (ጋራዥ) አገልግሎት እና
- የጀነሬተር ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ በጨረታው መወዳደር የምትችሉት፡-
- ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውንና የዘመኑ ግብር የፈለሱትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀውና አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ግብር የከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ጨረታ ለመሳተፍ፣ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚጫረቱበት የማይመለስ በብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አዲስ አበባ ስታዲየም መንገድ ትራንስፖርት ያለበት ተመሳሳይ ህንፃ ላይ በሚገኘው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ግዥና ፋይናንስ ዳይሬከቶሬት 3ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ስም ለሚጫረቱበት ሲፒኦ 5000 ብር ማስያዝ ይጠባቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ፖስታቸውን በማሸግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ካሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት ከተገለፀው አቅርቦት መጠን በላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው ውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሣይቀየር እስከ 25% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚቻል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፣
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር-0911065820/0913001666 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
አድራሻችን፡- አዲስ አባባ ስታዲየም መንገድ ትራንስፖርት ያለበት ተመሳሳይ ህንፃ ላይ ይገኛል::
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፖሊሲ ጥናት
ኢንስቲትዩት